Skip to main content
dijital sidaam

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ሰነድ ላይ የውይይት መድረክና የለሙ ሲስተሞች ምረቃ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንደገለፁት አገር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ካልታገዘች እድገት ማሳየት አትችልም በማለት ከብልፅግና መንገዶች አንዱ በቴክኖሎጂና በሳይንስ የበለፀገች አገር መገንባት ነው ብለዋል።

ቴክኖሎጂ ግዜና ሀብትን ከብክነት ለመታደግ ቁልፍ መሳርያ ነው ያሉ ሲሆን ሳይንስና ቴክኖሎጂን ፓርቲያችን በትኩረት ያየዋል ብለዋል።

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የስራ ክህሎት እና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃገረፂዮን አበበ እንደገለፁት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የተሳለጠ አሰራር ለመዘርጋት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀው ክልላችን በዲጂታል የተሳሰረ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል።

በስነስርዓቱ ላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የተሰሩ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።

የሲዳማ ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

ግንቦት 14-2015 ዓ.ም

ሀዋሳ