Skip to main content
"የክልላችንን አመራር ውጤታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እና የህዝባችንን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት የሚያስችል ችግር ፈቺ የሆነ የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሂደናል።" አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

"የክልላችንን አመራር ውጤታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እና የህዝባችንን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት የሚያስችል ችግር ፈቺ የሆነ የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሂደናል።" አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

የሲዳማ ክልል ሲያካሂድ የነበረው የ2016 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ።

በመድረኩ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የአመራር ስርዓት ለመፍጠር የተደረገው ጥረት ውጤት እያስገኘ መምጣቱን ገልፀው በተልዕኮው መነሻ ተግባራትን በውጤታማነት በመፈፀም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እና የህዝባችንን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት የሚያስችል ጥንካሬንና ድክመትን የለየ ጠንካራና ችግር ፈቺ የግምገማ መድረክ አካሂደናል ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው እንደገለጹት የክልሉን ህዝብ የኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራት ሲከወኑ እንደቆዩ በማንሳት አመራሩ በቀሪ ወራት የተጀመሩት ተግባራት ይበልጥ በማጠናከር እና የቀሩ ተግባራትን በማፋጠን ግባችንን ልንመታ ይገባል በማለት መመሪያ ሰጥተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው እንደገለፁት እንደ ክልል በጀት ዓመቱ ለመፈፀም ካቀድናቸው ስራዎቻችን መካከል ብዙዎቹ የተሻለ ውጤት የተገኘበትና እንደ አመራር በማቀድ ፣ በመፍጠን እና በመፍጠር ውጤታማ ስራዎችን ለመፈፀም ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልፀው የክልሉን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥና ዕቅዱን ለማሳካት የተደረገው የአመራር ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑን አንስተዋል።

በግምገማው ወቅት የተገኙት ተጨባጭ ውጤቶችና ካጋጠሙ ውስንነቶች እየተማርን ለላቀ ውጤቶች መስራት ይገባናል ብለዋል።

በመድረኩም ላይ የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጨምሮ የዞን እና የወረዳዎች የፊት አመራሮች በተገኙበት ተካሂዶ ተጠናቋል።

የካቲት 18-2016 ዓ.ም

ሀዋሳ