Skip to main content
"የአፊኒ" የፊልም ምረቃ ስነ-ስርዓት በሲዳማ ባህል አደራሽ  እየተካሄደ ነው

"የአፊኒ" የፊልም ምረቃ ስነ-ስርዓት በሲዳማ ባህል አደራሽ እየተካሄደ ነው

የሲዳማ ባህላዊ እሴት፣ ቋንቋውንና ታሪኩን በጉልህ እንዲያሳይ ታስቦ የተሰራው "የአፊኒ" የፊልም ምረቃ ስነ-ስርዓት በሲዳማ ባህል አደራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በስነስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የሀገራችን ዕውቅ አርቲስቶች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፊልሙን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት አፊኒ መደማመጥ ያለበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ነው ብለዋል። አፊኒ፤ አመፅ ይቀንሳል፣ አሳታፊነት ያላብሳል፣ የተረጋጋ ማህበረሰብ ይፈጥራል ያሉ ሲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ባህላዊ እሴት ቀደምት አባቶቻችን ጠብቀውት ለዚህ አብቅተዋል ብለዋል። አፊኒ የሀገር ሀብት የሚሆን ድንቅ ባህላዊ እሴት እንደሆነም ገልፀዋል። ትውልዱ ከአባቶች የተላለፈውን ድንቅ የሆነውን አፊኒ ስርዓትን ጠብቆ ሊያቆየው ይገባል ብለዋል።

የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃጎ አገኘው እንደገለፁት ፊልሙ የተለያዩ የሲዳማ ባህል ኩነቶችን ገልጸው ፊልሙ የሚዳስሳቸው አጠቃላይ የህዝቡን አኗናር አመጋገብ እንዲሁም የክልሉን መልከአ ምድር የዳሰሰ መሆኑን ገልፀዋል። በሲዳማ የግጭት አፈታት ስነስርአት ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነም ሃላፊው ጨምሮ ገልፀዋል።

የሲዳማ ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት