Skip to main content
News

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ የመኸር እርሻ ስራዎችን በማልጋ፣ ጎርቼ እና አርቤጎና ወረዳዎች የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸው ባስተላለፉት መልዕክት በቆላማ አከባቢዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተበላሸ ምርት በደጋማ አከባዎች በመኸር ምርት ለማካካስ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ በመግለፅ ከታቀደው በላይ መሰራቱን ገልፀዋል ። አክለውም የአፈርና ውሃ ጥበቃ መሰራቱ ለመኸር ምርት ከፍተኛ አሰተዋጽኦ እንዳለው በመግለፅ በበልግ ሰብል ወቅት በድርቅ ለተጎዱ አከባቢዎች በመኸር እንዲዘሩ የዘር አቅርቦት እንደቀረበላቸው በመግለፅ ለምግብ አቅርቦት ድጋፍ ለሚሹ አከባቢዎች የምግብ አቅርቦት እየቀረበ እንደሆነ ገልፀዋል።