Skip to main content
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የዩኤስ ኤድ ሚሽን ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር የሚመራ ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የዩኤስ ኤይድ ሚሽን ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር የሚመራ ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት የክልሉ መንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ ነድፍ እየተንቀሳቀሰ እና ለውጦች እየታየ እንደሚገኝና በዩኤስ ኤይድ ድጋፍ ከፍታ ድርጅትም ወጣቶችን በክህሎት፣ በኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ከባህርይ ለውጥ አኳያ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ገልፀው እየተሠራ ላለው ስራ የዩኤስ ኤይድ ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አራርሰው ገረመው በክልሉ በአጠቃላይ ኢኮኖሚክ ተግባራት ሁኔታ ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አይነተኛ ሚና እንዳላቸው በማብራራት በተይም በክልሉ በዩኤስ ኤይድ ድጋፍ ሰባት ፕሮጀክት እየተተገበሩ እንደሆነ ተናግረው ለእነዚህ ፕሮጀክቶች የተመደበውን ገንዘብ ለተመደበለት ዓላማ እንዲውል ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እያስፈፀመ እንደሆነ ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከልዑኩ ጋር በነበራቸው ቆይታ በዩኤስ ኤይድ ወጣቶችን መሰረት አድርጎ በተሰሩ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ በክልሉ መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ የተሰጣቸው ስራዎች በጋራ ለመስራት እና በቀጣይ በክልሉ የትኩረት መስኮችን መነሻ ባደረገ ጉብኝት በማድረግ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል፡፡

የሲዳማ ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

መስከረም 23-2016 ዓ.ም

ሀዋሳ