Skip to main content

           ዓላማ

የክልሉ ህብረተሰብ የሚያቀረባችዉ አስተዳደራዊ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፈጣንና ፍትሐዊ ዉሳኔ እንዲያገኙ ማድረግ፤ በክልሉ ዉስጥ የሪፎርም ፕሮግራሞች በአግባቡ ተተግብረዉ ህብረተሰቡ ሰላምና  ፀጥታዉ ተረጋግቶና መልካም  አስተዳደር  ስፍኖ የክልሉ ህዝብ ከአካባቢዉ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ነዉ፡፤

የመልካም አስተዳደርና አካባቢ ጉዳዮች ጽ/ቤት የሚሰጣቸዉ ዋና ዋና አገልግሎቶች

  • አስተዳደራዊ ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን መቀበል፣ማጣራትና ዉሳኔ የመስጠት ስራ፣
  • የመልካም አስተዳደር ፖኬጆች አተገባበርና ዉጤታማነትን በተመለከተ የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት የማከናወን ስራ፣
  • የሪፎርም ኘሮግራሞች ጉዳዮችን አተገባበር የመከታተል፣ የመደገፍና ግብረ-መልስ የመስጠት ስራ፣
  • ሁሉም የለውጥ (Reform) ኘሮግራሞች ተቀናጅተዉ እንዲመሩ የንቅናቄ መድረክ የመፍጠር ስራ፣
  • የመልካም አስተዳደር ችግሮች በጥናት መለየትና መፍትሔ መፈለግ
  • የልማትና የመልካም አስተዳደር አፈጻጸሞችን መከታተልና መደገፍ ስራ መስራት
  • የቅሬታና አቤቱታ መንስኤዎችና በተገልጋይ እርካታ ዙሪያ የጥናት ስራ፣
  • በየደረጃዉ የሚገኙ የቅሬታና አቤቱታ መዋቅሮችን የመከታተልና የመደገፍ ስራ፣
  • በየደረጃዉ የሚገኙ የቅሬታና አቤቱታ መዋቅሮች ላይ የሚሰሩ ፈፃሚዎችን አቅም የማሳደግ ስራ መስራት ፡፡