ተልዕኮ
ሴክተሩ በክልሉ ያሉትን ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ሀብቶች አቀናጅቶ በመምራትና ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት ጥቅም ላይ በማዋል፣ የክልሉ ህዝቦችን አንድነት በማጠናከር፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በማፋጠን መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንዲጎለብት ማድረግ፡፡
ራዕይ
በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ተረጋግጦ እና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ዘላቂ ልማትን በማምጣት 2022 ዓ.ም በለፀገና መካከለኛ ገቢ ያለዉ ህብረተሰብ ተፈጥሮ ማየት፡፡
ዓላማ
ሴክተሩ አደረጃጀቱንና አሰራሩን በማሻሻል ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የሚሰጠዉን አገልግሎት ወጥ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ጥራት ያለዉና ወጪ ቆጣቢ ለማድረግ የሚያስችሉ ማድረግ ነዉ፡፡
የተቋሙ ስልጣንና ተግባር
የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በባህሪዉ ከሌሎች ሴክተሮች በተለየ አግባብ የሚታይ ከመሆኑ አንፃር የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 61 ለጽ/ቤት የተሰጠዉ ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉ ህገ- መንግስት ለመስተዳድር ምክር ቤቱና ለርዕሰ መስተዳድሩ በአንቀጽ 57 እና 59 የተሰጡ ስልጣንና ተግባራትን ከማስፈፀም አኳያ ርዕሰ መስተዳድሩን በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚደግፉ፣ ዝርዝር ጥናት በማድረግ የዉሳኔ ሀሳብ የሚያቀርቡ እና የሚያማክሩ እንዲሁም መስተዳድር ምክር ቤቱን የሚደግፉ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን ያሉት ሲሆን በዚህም መሰረት፡-
- የርዕሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በመሆን ጭምር ስለሚያገለግል፣
- በክልሉ ምክር ቤትና በፌዴራሉ መንግስት የወጡ ህጎችና የተሰጡ ዉሳኔዎች በክልሉ ዉስጥ በስራ መተርጎማቸዉን በማረጋገጥና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ለዉሳኔ የማቅረብ፣
- በሕግ በሚወሰነዉ መሰረት የክልሉን መስተዳድር ምክር ቤት፣ ሌሎች አስፈፃሚ አካላትና ልዩ ልዩ ተቋማትን የማደራጀት፣ የመቆጣጠርና የመምራት፡
- የክልሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የመንደፍ፤ የህግ ረቂቆችን ለክልሉ ምክር ቤት አቅርቦ የማስፀደቅ፣ የተወሰነዉንም የማስፈፀም፣
- በክልሉ ዉስጥ ሕግና ሥርዓት መከበሩን የማረጋገጥ፣
- የክልል ምክር ቤት በሚሰጠዉ ስልጣን መሰረት ደንቦችን የማውጣት፣
- የርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን መንግስት ምክር ቤት የመምራት፤ የማስተባበርና የመወከል ስራዎችን የማሳለጥ፣
- የክልሉ መስተዳድርና ምክር ቤት ያወጣቸዉን ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና ዉሳኔዎችን ተፈፃሚነት የመከታተልና ሪፖርት የማቅረብ፣
- የክልሉን ደህንነት ለመጠበቅና ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የተቋቋሙትን ክልል አቀፍ የፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች በበላይነት የመከታተል፣ የመደገፍና የመቆጣጠር፣
- በክልሉ በተዋረድ የሚገኙትን የአስተዳደር እርከኖች ሥራዎችን የመምራትና የመቆጣጠር ኃላፊነቶች አሉት፡፡
- የመስተዳድር ምክር ቤቱን የስብሰባ ሂደቶች በመቅረፀ-ምስል፣ መቅረፀ-ድምፅና በህትመት ሠነዶችን በአግባቡ በመያዝና በመጠበቅ ለሚፈቀድላቸዉ አካላት የማቅረብ ስራ፣
- የመስተዳድር ምክር ቤቱን ቃለ-ጉባዔ መያዝ እና የሚተላለፉ ዉሳኔዎች ምስጢራዊነታቸዉ ተጠብቆለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ፣
- ለካቢኔ የሚቀርቡ ጉዳዮች በመስተዳድር ም/ቤት የአሰራር ደንብ መሰረት ተገቢውን የጥራት ደረጃ ጠብቀው መቅረባቸውን የማረጋገጥ አገልግሎት፡፡
- የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የሚያፀድቃቸዉን ደንቦችና መመሪያዎች አሳትሞ የማሰራጨት ስራ፣
- ከመንግስት መ/ቤቶች ለመስተዳደር ም/ቤት ውሳኔና ውይይት የሚቀርቡ ሰነዶችና የውሳኔ ሀሳቦችን በተመለከተ የማማከር፣ ድጋፍ የመስጠትና የማስተባበር ስራ፣
- በመስተዳድር ም/ቤቱ ለሚቋቋሙ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ድጋፍ የመስጠትና የማስተባበር ስራ፣