Skip to main content

    ዓላማ

የጽ/ቤቱ ዓላማ የክልሉ መንግሥት በተለይ አስፈጻሚው አካል፤በክልሉ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት፣እንዲሁም ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለውን ልማት ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት የበኩሉን ቁልፍ ሚና በመጫወት ተገልጋዩ ህብረተሰብ የተፋጠነ፣ጥራቱን የጠበቀ፣ወጪ ቆጣቢና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኝ መከታተል፣መደገፍና ማማከር ነው፡፡

 አማካሪዎች ጽ/ቤት የሚሰጣቸዉ ዋና ዋና አገልግሎቶች

  • የአስፈጻሚውን የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ የመገምገምና ለሚመለከተው አካል የማቅረብ ስራ፣
  • የአስፈፃሚውን የዕቅድ አፈጻጸም የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የመገምገም እንዲሁም ለሚመለከተው አካል የማቅረብ ሥራ፣
  • ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው የኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊና የመሰረተ-ልማት ጉዳዮችን የመመርመር፣ የማጥናት፣ መፍትሔ እንዲያገኙ የማድረግና አፈፃፀማቸውን የመከታተል ስራ፣
  • ለዕቅድ አፈጻጸም እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ክፍተቶችን በጥናት የመለየት እና የመከታተል ስራ፣
  • በሚመለከታቸው የክልሉ ተቋማት የተከናወኑ ወሳኝ ተግባራትን በመለየት የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት እንዲከናወን የማስተባበር ስራ፣
  • የህግ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲያገኙ የማጣራት ስራ፣
  • የሰብአዊ መብቶች አያያዝና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንዲሻሻል የሚያስችል አሰራር እንዲኖር የማድረግ ስራ፣
  • ረቂቅ ህግ የማዘጋጀትና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ፣
  • የሌሎች ተቋማትን ረቂቅ ህጎች መሰረታዊ የህግ መርሆዎችን የተከተሉ መሆናቸዉንና አስፈላጊነታቸዉን የማጣራት ስራ፣
  • በህግ ጉዳዮች ላይ ለመስተዳድር ም/ቤቱም ሆነ ለርዕሰ-መስተዳድሩ  ተገቢውን ሙያዊ  አስተያየትና አማራጮችን የማቅረብ ስራ፣
  • የፍትህ ስርአት ማሻሻያ ፕሮግራም በሚመለከታቸው ተቋማት ተቀናጅቶ ሊተገበር በሚችልበት ሁኔታ መታቀዱንና መከናወኑን የመከታተልና ግብረ መልስ የመስጠት አገልግሎት፣
  • የፀጥታ ሴክተሩን አፈፃፀም በበላይነት የመምራት፣ የመከታተል፣ የመደገፍና የመቆጣጠር ስራ፣
  • በአጎራባች ክልሎች ድንበር አካባቢዎች የሚኖረውን የሠላምና የልማት እንቅስቃሴ በቅንጅት የማከናወን አገልግሎት፣
  • አጠቃላይ የፀጥታ ሪፖርት በመቀበልና ትንታኔና ዕንድምታዎችን ለይቶ የመደገፍ ስራ መስራት